የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ
By SBS
ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።
Latest episode
-
"ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ
አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Mark… -
"የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁ
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ። -
ሶስና ወጋየሁ፤ ከአውስትራሊያ ጥገኝነት ጥየቃ ለክብር ሽልማት መብቃት
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ እንደምን በሀገረ አውስትራሊያ ከጥገኝነት ጥየቃ ለከፍተኛ የክብር ሽልማት እንደበቁ ያወጋሉ። -
ሶስና ወጋየሁ፤ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሀገረ አውስትራሊያ
ሶስና ወጋየሁ፤ ስርከስ ኢትዮጵያ ካፈራቸው ምርጥ ኮከቦች አንዷ ናቸው። ከሜክሲኮ አደባባይ ውልደትና ዕድገታቸው እስከ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃ ሕይወታቸው ያወጋሉ። -
" 'ሞቷል' የሚባለው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር እንደተነሳ የምናሳየው የምንሠራቸውን ነገሮች በማሳየትና ተጠያቂም በመሆን ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ የበጎ ፈቃደኛ አገልጋይነትን ፋይዳዎች በማመላከት ጥሪዎችን ያቀርባሉ። -
"በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን የምንል ከሆነ፤ የግል የፖለቲካ አቋማችንና ሃይማኖታችንን ሳናንፀባርቅ ወደ አንድነት እንምጣ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለማኅበረሰብ አገልጋይነት ገፊና ሳቢ የሆኗቸውን አስባቦች፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን ያወጉት 'ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ' ግለ ታሪካቸው ተከታይ አድርገው ይናገራሉ። -
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው የወቅቱ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ናቸው። ከውልደት ሥፍራቸው ጎንደር ከተማ እንደምን ለሀገረ አውስትራሊያ እንደበቁ ግለ ታሪካቸውን አጣቅሰው ያወጋሉ። -
"መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው። -
ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል። -
"ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።